የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝራስ አሞራው 3ኛ ኮር/Ras Amoraw core, Debe Telemte Tekezie Division victory
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ራስ አሞራው 3ኛ ኮር
አስደሳች ድል!
አንድ ዲሽቃ ሞተራይዝድ የጦር መሳሪያ ተማርኳል!
የዛሬ አመት ደባርቅ ከተማ ሁለት ዲሽቃና አንድ ሞርተር ማርከው ጀግንነታቸውን ያስመሰከሩት የድብ ጠለምት ተከዜ ክ/ጦር ነበልባሎች ልማደኞቹ ዛሬም ዲሽቃ በመማረክ ደግመውታል።
ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለ ጦር ለሁለት ቀን ተከታታይ ውጊያ አድርገው የጠለትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው አፍርሰውታል ።ከ45 በላይ ሲደመሰስ ቁጥሩ ያልተረጋገጠ ቆስሏል።6 ስቃጥላ የዲሽቃ ተተኳሽ ጥይቶችን ጨምሮ በርካታ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ጠላት በመደምሰስ መማረክ ተችሏል።
በርካታ የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያም ከምርኮኛ የብርሃኑ ጁላጦር ትከሻ በክንዳችን ማርከነዋል።
አፋብኃ /AFNF
ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ