ከዋርካው ምሬ ወዳጆ የተሰጠ መግለጫ

ከዋርካው ምሬ ወዳጆ የተሰጠ መግለጫ

ትግላችን የአብይ አህመድ አረመኔውን ሰራዊት በመደምሰስ የአማራን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ነው።

ዛሬ ነሃሴ 03-12-2017 ዓም እንደ ድርጅት ምኒልክ ዕዝ በ5 ኮሮች ከባድ ትንቅንቅ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን በአውደ ውጊያ ውሎም በጠላት ላይ በርካታ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰንበታል!!

ጠንካራው ሰራዊታችን በጠላት አረመኔው ሰራዊት ላይ ውጊያውን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በተለይም ምኒልክ ዕዝ በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉም ኮሮች በተመሳሳይ ስዓት እና ጊዜ በአንድ ማዕከላዊነት ውጊያውን መጀመራችን ያስፈራው አገዛዙ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመሆኑ የብልፅግናውን ፕሮፓጋንዳ ባዶ የሚያስቀረው ዕለታዊ ተጋድሎዎችን በተከታታይ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ዕለት ለተገኘው ድል በእጅጉ እናመሰግናለን ብሏል ዋርካው ምሬ ወዳጆ

የፋሺስት አብይ አህመድን ስርዓትን ነቅለን ለመጣል የምናደርገው ተጋድሎ ይበል የሚያሰኝ ነው።

አውደ ውጊያው በሁሉም ኮሮች ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ውጊያውን በስነ ልቦና የበላይነት በመውሰድ በጠላት ላይ ነገም እንደ ዛሬው የመደምሰስ፣የማስከዳት፣ከቦ የማጥቃት እና ዕግር ነቅሎ ሲሸሺ የመማረክ ተጋድሏችን ይቀጥላል ብሏል!!

እኛ የምንታገለው ህዝባችን ነፃ ለማውጣት አስከሆነ ድረስ ነፃ ህዝብ እና ነፃ መሬት እስከምንፈጥር ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል!!

መላው የአማራ ህዝብም ሃሳባችንና እውነተኛ ትግላችን መሬት ነክቶ እውን እንድሆን ዛሬም እንደ ትናንትናው ከጎናችን እንዲትሆን አደራ ማለት እፈልጋለሁ!!

በህዝብ ትብብር እና ሁለንተናዊ ድጋፍ ሰራዊታችን ላስመዘገባቸው ድሎች መላው የአማራ ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ!!

በመጨረሻም የተጠናከረው ውጊያ በሁሉም ኮሮች እና ግንባሮች የሚቀጥል ሲሆን በራያ፣በመሃል ወሎ ቀጠና፣በላስታ እና በምዕራ ወሎ ግንባር ሁሉም ኮሮች እና ክ/ጦሮች የሚሳተፉበት አውደ ውጊያ የሚቀጥል ይሆናል!!

በአጠቃላይ ዛሬ ላስመዘገብነው በዓይነቱ ለየት ያለውን አውደ ውጊያ ለመራችሁ፣ላስተባበራችሁ እና ሃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ አመራሮች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት መልዕክቱን ያስተላለፈ ሲሆን በየደረጃው ያለ ደጋፊ አመራርም የአውደ ውጊያን አጠቃላይ ሁኔታ ከስር ከስር እየተከታተለ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ስራችሁን እንድትፈፅሙ ሲል ትዕዛዙን አስተላልፏል!!

የብልፅግና አሸባሪ ሃይል የሰራዊታችንን አቅም ከምስራቅ አማራ እስከ አሁኑ አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ድረስ የማድረግ እና የመፈፀማችንን ብቃት ጠንቅቀው የሚያውቁ ቢሆንም ታሪካዊ ተጋድሏችንን እና ጀግንነታችን ለማስተባበል የሞከሩበትን ሁሉን አቀፍ ትርክትም በምናካሂደው እውነተኛ ውጊያ ማሳየታችን እንቀጥላለን በማለት የዕለቱን የአውደ ውጊያ ውሎ አስመልክቶ መልዕክቱን አስተላልፏል!!

መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ትግል ያሸንፋል!!

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!

አርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ

የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ አዛዥ

ነሃሴ03-12-2017 ዓም

Previous
Previous

አፋብኃ በጎንደር፤ በወሎና በሸዋ ቀጠናዎች የአማራ ፋኖ የአውደ ውጊያ ውሎና የዕለቱ የግንባር መረጃዎች በተመለከተ በአርበኛ ዮሃንስ ንጉሱ የቀረበ

Next
Next

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝራስ አሞራው 3ኛ ኮር/Ras Amoraw core, Debe Telemte Tekezie Division victory