አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አባ ናደው የተገኙ ድሎችን አስጠብቆ አዳዲስ ድሎችንም እያስመዘገበ ቀጥሏል! /Abebe Fentaw-AFNF’s Spoke Person
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አባ ናደው የተገኙ ድሎችን አስጠብቆ አዳዲስ ድሎችንም እያስመዘገበ ቀጥሏል!
በሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎችና ታዳጊ ከተሞች:ኮን፣እስታይሽ፣ሃሙሲት፣አሁንተገኝ፣ ቀበሮ ሜዳ እና ሌሎች ታዳጊ ከተሞች በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ገብተዋል:: እነዚህ ድሎች እየተመዘገቡ ያሉት አዲስ በተደራጀው በኮሩ ሰብሳቢ በሻለቃ ሃብቴ እባቡ እና በወታደራዊ አዛዡ አርበኛ ተመስገን አለባቸው የሚመራው የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች ሲሆን የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃድ የሆነችው 5ኛ ሻለቃም የበኩሏን ጉልህ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች::
ተጋድሎው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ዳውንት ወረዳ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: ደላንታ ወረዳ ከወረዳ መቀመጫው ወገልጤና ከተማ ውጭ ሙሉ ለሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው:: መቄትና ጋሼና ከከተሞቹ ውጭ ያሉ ቀበሌዎች 100% በምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ናቸው:: ሌሎች ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎችም በቅርቡ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ይሆናል::
ከዘመቻ አባናደው በድል መጠናቀቅ በኋላ በርካታ ቁጥር ያለው እግረኛና ኮማንዶ ሰራዊት ወደ ቤተ-አማራ በማስገባት በመካናይዝድና በአየር ሃይል በጄትና በድሮን ታግዞ በሙሉ አቅም ወደ ማጥቃት የገባውን የፋሽስቱን ሰራዊት ምሽግ ለቆ ወደ ፋኖ ቀጠናዎች እንዲገባ በማድረግ በአውደ ውጊያ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም በመማረክ ከአውደ ውጊያ ውጭ በማስኮብለል ብትንትኑን እያወጣነው እንገኛለን::
ፋሽስቱ ብልፅግና በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ እና ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ምስራቃዊ ቀጠናዎች እስከ አፋር አጎራባች አካባቢዎች ባለፉት አምስት ቀናቶች ከባድ ማጥቃት ቢያደርግም በምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በኮሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ደባሽ መምሬ እና በኮሩ ዘመቻ አርበኛ እንድሪስ ጉድሌ አጋፋሪነት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው አሳፍረው በዘረራ ቀጠናውን ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም