ለመላው የአማራ ህዝብ፤ ለመላው የፋኖ አባላትና አመራሮች በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የተሰጠ መግለጫ
(የቋራ ቃል ኪዳን)
የአማራ ህዝብ የጀመረው የህልውና ተጋድሎ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋጋለበት ዘመን ላይ እንገኛለን:: የአማራ ክልልን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተደረገ ያለው የህልውና ትግል ህዝባዊ መሰረት ያለው በመሆኑ በአንድ ወጥ ድርጅት እየተመራ ባይሆንም አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል።
ትግሉ ግለቱን ጠብቆ የበለጠ እንዲፋፋም እና በአጭር ጊዜ የአማራን ህዝብ ነፃነት ያረጋግጥ ዘንድ ይህንን ትግል የሚያቀናጅ እና የሚያስተባብር የጋራ አመራር ያለው ድርጅት መወለድ ግዜው የጠየቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ተገኝቷል። ይህንን አንገብጋቤ ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል፥ ብዙ ውጣ ውረዶችም ታልፈዋል።
በመጨረሻም የአማራ ህዝብ የናፈቀው፣ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የተመኘው፣ መላው የፋኖ ሰራዊት የጠበቀው፣ ታሪክ እንዲፈፀም የጠየቀው ጉዳይ ተጠናቋል። የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ - አማራ)፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የአማራ ፋኖ በሸዋ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ቋራ-ጎንደር ባደረጉት ቀናትን የወሰደ መስራች ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 01 ቀን 2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (Amhara Fano National Force) የተሰኘ ድርጅት መመስረታቸውን ለመላው ሰራዊታችን፣ ለአማራ ህዝብ እና ለትግሉ ደጋፊዎች እናበስራለን። መላው የትግላችን ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በአማራ ብሔርተኝነት የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም ላይ የቆመ ህዝባዊ ተጋድሎ የሚመራ ሲሆን የድርጅታችን ዋነኛ ተልዕኮም እየተደረገ ያለውን የህልውና ትግል እና ህዝባዊ አብዮት ማስተባበር እና ማቀናጀት ይሆናል።
ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በኢትዮጵያ ሉዓላዊትና አንድነት ላይ የማያወላውል አቋም ያለው ሲሆን የአማራ ህልውና የሚረጋገጠውም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ኃይሎች ጋር በሚደረግ የጋራ ትግል የአብይ አህመድን የሽብር አገዛዝ በማስወገድ በምትኩ በሽግግር ሂደት በሚገነባ የጋራ መንግስት ምስረታ እንደሆነ ያምናል።
ድርጅታችን የአማራ ህዝብ ተጋድሎ የህልውና ተጋድሎ ነው ስንል ህልውናችንን የተፈታተነውን መዋቅር እና ትርክት መለወጥ
እንደሆነ በፅኑ እንደማመናችን መጠን የወልቃይት፣ ጠለምት እና ራያን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢ ያለ የወሰን፣
የማንነት እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ለማስመለስ እንደሆነ እናረጋግጣለን።
መዋቅራዊ ጥቃትን መቀልበስ እና ለአማራ ህዝብ ማህበራዊ ፍትህን የሚያሰፍን ስርዓተ-መንግስት መፍጠርን ታሳቢ ያደረገውን
ትግል የሚመራ ማዕከላዊ አመራር መፈጠሩ የህልውና ትግል እያደረገ ላለው ህዝብ ተጨማሪ አቅም ነው። ድርጅታችን በሙሉ
አቅሙ ትግሉን እንዲመራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ይፈልጋል።
A.F.N.F. 1አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) Amhara Fano National Force (AFNF) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አወቃቀር ጠቅላላ ጉባኤ፣ ማዕከላዊ ምክር ቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሁም የአባት
አርበኞች ምክር ቤትን አካቶ ሕገ ደንብ በማፅደቅ ተቋቁሟል። የአባት አርበኞች ምክር ቤትን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ
እንዲመሩት መስራች ድርጅቶቹ ተስማምተዋል።
የድርጅቱን አመራር በተመለከተ:-
የመስራች ድርጅቶችን አባላት እና ሰራዊት ለማዋሃድ ጊዜ በማስፈለጉ፤ የድርጅቱን አመራር በማዋቀር ሂደት የመስራች
ድርጅቶችን አመራር እና አባላትን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ሲባል፤ የትጥቅ ትግሉ ከሚደረግበት የቀጠና ስፋት አንፃር የጋራ
አመራር በማስፈለጉ፤ እንዲሁም ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፋኖ አደረጃጀቶች የድርጅቱ አካል የሚሆኑበትን እድል
ለመፍጠር ሲባል ድርጅቱ በማዕከላዊ ኮማንድ እንዲመራ ተወስኗል። በመሆኑም 13 አባላት ያሉት ማዕከላዊ ኮማንድ የተቋቋመ ሲሆን አባላቱም:-
1ኛ. አርበኛ ዘመነ ካሴ
2ኛ. አርበኛ ሐብቴ ወልዴ
3ኛ. አርበኛ ምሬ ወዳጆ
4ኛ. አርበኛ ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ
5ኛ. አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
6ኛ. አርበኛ ሔኖክ አዲሴ
7ኛ. ጀነራል ተፈራ ማሞ
8ኛ. አርበኛ ዝናቡ ልንገረው
9ኛ. አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ
10ኛ. አርበኛ አስቻለው በለጠ
11ኛ. አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል
12ኛ. አርበኛ ማርከው መንግስቴ
13ኛ. አርበኛ አከበር ስመኘው
ሙሉ የአመራር ምደባ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ማዕከላዊ ኮማንዱ የድርጅቱን የፖሊት ቢሮ እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚና በመውሰድ የድርጅቱን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ የዲፕሎማሲ እና የአስተዳደር ስራዎች እንዲመራ እና እንዲወስን ስምምነት ላይ ተደርሷል። ለመላው የአማራ ህዝብ፤ ለመላው የፋኖ አባላትና አመራሮች በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን
የሚከተለውን ጥሪ እናስተላልፋለን።