ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ሁለት ኮሮች ውጊያ ከፍተዋል!
ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም
ረፋድ 5:00
4ኛ ኮር... በመፈራረስ ላይ የሚገኘው የዓብይ አገዛዝ ሰራዊት ዛሬ በዋት ከጎንደር ከተማ፣ከሙሴባምብ ከሳንጃና ከሶሮቃ ለቃቅሞ ያሰባሰበውን በመኪና በመጫን ወደ ጠረፋማው ቀጠና አብርሃጅራ ከተማ አቅጣጫ ጉዞ የጀመረ ቢሆንም ሶሮቃን እንዳለፈ እርጎየ ላይ የደጃዝማች 4ኛ ኮር የተወጣጣ የሰራዊት አሃድ የመግደያ መሬት አስገብቶ በደፈጣና በፊት ለፊት ውጊያ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሶበታል።
ወደ ምዕራብ ለመጓዝ የነበረው ዕቅድ ከሽፎበት ቁስለኛና ሙት አዝረክርኮ ወደ መጣበት ለመመለስ ቢሞክርም በ4ኛ ኮር
ጥምር መች ኃይል በሌላ በኩል ስለተቆረጠ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ጣረሞት ላይ ይገኛል።
4ኛ ኮር...ወደ ምዕራብ ሲጓዝ የነበረው ጠላት እርጎየ ተቆርጦ እየተቀጠቀጠ በመሆኑ ከድምሰሳ ለመታደግ ተልዕኮ ይዞ ከአብራሃጅራ ከተማ ተነስቶ ወደ እርጎየ የገሰገሰው የብይ ዙፋን አስጠባቂ ታጣቂ ምስላል የተሰኘ ቦታ በ4ኛ ደጃዝማች ኮር የደፈጣ መች ሰራዊት ተቆርጦ የእሳት ዝናብ እየዘነበበት ይገኛል።ሰብሮ የውጊያ ድጋፍ አድርጎ ሊታደግ የመጣው ወራሪ ሰራዊት በዚህ ሰዓት ክፉኛ እየተደቆሰ ነው።ሙሉ በሙሉ ከመደምሰስ ወይም እጅ ከመስጠት ሌላ የዕድል ቀዳዳ አይኖረውም።
2ኛ ኮር...ዛሬ ነሃሴ 08/2017 ዓ.ም ንጋት ቋራ ወረዳ በሙር ከተማ አቅራቢያ የሰፈረው የጠላት ሰራዊት በመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላና አድዋ ክ/ጦር ጥምር ብርጌዶች ወታደራዊ ማጥቃት እየተመታ ነው።ንጋት በሞርተሮች ድብደባ የተጀመረው ማጥቃት አሁንም ቀጥሏል።በዚህ የቋራ ግንባር ውጊያ በተመሳሳይ ጠላት ሰብዓዊ ጉዳት እየደረሰበት ሲሆን የመይሳው 2ኛ ኮር ሰራዊት የግዳጅ ተልዕኮ አርበኛ ሚናስ አለማየሁ ከበላይ ዘለቀ ዕዝ ወታደራዊ አመራሮችና ዘመቻ ጋር በመጣመር የግንባሩን ግዳጅ አብሮ እየመራ ይገኛል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሰኔ 08/2017 ዓ.ም
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ