ዛሬም እንደ ትናንቱ ታላቅ ድል የፈፀሙት የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ

የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ታሪካዊቷ ጉና ክፍለጦር፣ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣ጣና ገላዉዲወስ ክፍለጦር እና ነበልባሉ ፎገራ ክፍለጦር በደቡባዊው ጎንደር ቀጠና ከፍተኛ ድል ተቀዳጅተዋል።

የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለጦር አንበሳዉ እስቴ ዴንሳ ብርጌ፣አንዳቤት ብርጌድ፣ሀገረ ቢዘን ብርጌድ፣መቅደላ ብርጌድ ፣የጉና ክፍለጦር ቃኝ እና መሀንዲስ እንዲሁም የጉና ክፍለጦር አመራሮች እና የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር አመራሮች የተሳተፉበት አዉደዉጊያ ተደርጎ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል።

ዛሬም እንደ ትናንቱ ታላቅ ድል የፈፀሙት የጉና ክፍለጦር የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ከጧቱ 12:00 ጀምሮ ከአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ፊት ለፊት የጨበጣ አዉደዉጊያ በማድረግ ሶስት የክንክሬት ምሽግ በመሰባበር ጠላትን ሙሉ ለሙሉ ደምስሰዉታል።

አዉደዉጊያዉ በእስቴ መካነየሱስ ከተማ፣በደንጎልት፣በዮቅራሀ እና ጌጣ አድማሱን አስፍቶ የተካሄደ ሲሆን በዮቁራሀ፣ቄጣ እና ደንጎልት የፈረጠጠዉ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።በዚህ አዉደዉጊያ የሀገረ ቢዛን ብርጌድ እና የአንዳ ቤት ብርጌድ አንድ ሻለቃ በጋራ ተሳትፈዋል።

የጉና ክፍለጦር አመራሮች እና የኮሩ አመራሮች በጋራ በመሆን አዉደዉጊያዉን የመሩት ሲሆን የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ፣የሀገረ ቢዘን እና የአንዳቤት ብርጌድ አመራሮችም ዉጊያን በጥበብ እና ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ መርተዉታል።

ከከተማዋ ዉጭ የነበረዉን የጠላት ኃይል በማፅዳት በአፋጣኝ እስቴ መካነየሱስ ከተማን የተቆጣጠሩት የጉና አናብስቶች በከተማ የሰፈረዉን እና አመራር ሲጠብቅ የነበረዉን የአገዛዙን ጡት ቆራጭ ቡድን ድባቅ መተዉታል።

መካነየሱስ ከተማን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር የታሰሩ እስረኞችን ማስፈታት የተቻለ ሲሆን ከታሰሩት መካከል አስር ቀን ያልሞላት እመጫት በአገዛዙ በግፍ ታስራ ዛሬ በልጆቾ የበረታ ክንድ ተለቃለች።በተጨማሪም አገዛዙ ስለሚሊሺያ ቀለብ ከዝኖ ያስቀመጠዉ ሎጀስቲክ በጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ልጆች ቁጥጥር ስር ዉሏል።

በአጠቃላይ በርካታ የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን ሶስት ብሬን እና ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ምርኮ ተደርጓል።ከሞት የተረፈ ከ130 በላይ የጠላት ኃይል ምርኮኛ ተደርጓል።ቁጥሩ ከ100 በላይ የሚሆን የጠላት ኃይል ደግሞ ተደምስሷል።

በዚሁ ቀጠና የአንዳ ቤት ብርጌድ አንዳቤት ከተማ በመግባት በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሟል።ጠላት በጀግኖቹ የአንዳቤት ብርጌድ ከበባ ዉስጥ ገብቱ ነፍስ ዉጭ ነፍስ ገቢ ሲል ዉሏል።ሌላኛዋ የጉና ክፍለጦር መቅደላ ብርጌድ ወደ እስቴ መካነየሱስ ሲጓዝ በነበረዉ የጡት ቆራጩ የበሰልፅግና ሰራዊት ላይ በሶስት የተጠና ቦታ ደፈጣ በመጣል አብዛኛው ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል።በተጨማሪም በጋሳኝ ከተማ በመግባት በርካታ የሚሊሺያ ኃይል በመደምሰስ ቀሪዉን ደግሞ ምርኮኛ ማድረግ ችለዋል።

በሌላ መረጃ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣የጣና ገለዉዲወስ እና የነበልባሉ ፎገራ ክፍለጦር ከደራ ሀሙሲት ከአርብ ከተማ በመዉጣት ወደ እስቴ መካነየሱስ ጉዞ በማድረግ ላይ በነበረዉ የጠላት ኃይል ላይ እርምጃ በመዉሰድ በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል።ጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ልጆች ከአርብ ገብያ የወጠዉን ኃይል ድባቅ በመምታት ወደ መጣበት አሳፍረዉ መልሰዉታል።

በዛሬው አዉደዉጊያ ከፍተኛ ድል የተገኛ ሲሆን ከሰሞኑ በአገዛዙ በጭካኔ የታረዱ እህቶቻችን ደም ተመልሷል።በዛሬዉ አዉደዉጊያ አንድነት የታየበት ሲሆን የራስ ተራራው ጉና ክፍለጦር የጠላትን መንገድ በመዝጋት የጠላትን አቅጣጫ ማደናቀፍ ችለዋል።በተጨማሪም የጀኔራል ሀይሌ መለሰ ክፍለጦር በስማዳ ወገዳ ከተማ በመግባት ታላቅ ድል ፈፅሟል።

በዚህ አዉደዉጊያ በርካታ ጀብዶች የተገኙ ሲሆን የድሎችን ዉጤት ከሚመለከተዉ አካል ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

©ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!

Previous
Previous

ጎጃምና ወሎ ከባድ ው.ጊያ |በጎንደር ከባድ ውጊያ እስቴ ከተማ የፋኖ ኃይሎች ተያዘየፋኖ አበበ መግለጫና የአራቱም ቀጠና ጡት ቆ.ረ.ጣ

Next
Next

በአማራ ፋኖ ትግል ያልተነገሩ እውነቶች |ከፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ጋር