ሻለቃ Mulatie Sisay

ሻለቃ Mulatie Sisay

ለመላው የምእራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ በየደረጃው ላላችው አመራሮች፣ የትግል አጋሮቸ እና ለመላው የጎጃም ህዝብና የትግላችን ደጋፊዎች ከሁሉ አስቀድሜ አማራዊይና ወንድማዊ ሰላምታየ በያላችውበት ይድረሳችው ማለት እፈልጋለው!!!!

ወራሪውና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን መንግስት መር እና ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል፣ ሃብትና ንብረት ዘረፋ እና ማውደም፣ አማራነትን የመፀየፍና የማጥፋት እኩይ ተግባር በመቃወም ከነበርኩበት የቀድሞው የመከላከያ ሰራዊት፣ ከወቅቱ የአብይ አህመድ የግል ካንፓኒ ከአባልነትና አመራርነት ለቅቄ በመውጣት የአማራን ህዝብ ትግል በቀድሞው የአማራ ፋኖ በጎጃም የአሁኑ ቴወድሮስ እዝን ተህሳስ 12/ 2017 ዓ/ም ተቀላቅየ የምችለውን ሞያዊይና አማራዊ ግዴታየን ድርጅቱ የሰጠኝን ተልእኮ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ተንቀሳቅሸ የምችለውን ሁሉ አስተዋፅኦ ሳደርግ ሙቆየቴን መግለፅ እወዳለው።

ለእውነት ይህ አንድ አመት ቆይታየ በህይወት ዘመኔ አይረሴው ትዝታየ፣ ታሪኬ መሆኑን በህይወት እስካለው የምናገረው፣ ሲመቻችልኝም የምፅፈው ልዩ የህይወቴ ምእራፍ መሆኑን መቸም አልዘነጋውም።

እንደ ድርጅት አመራር፣ እንደ ታጋይ ብሎም እንደ ህዝብ ላደረጋችውልኝ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ ከውስጤ ፍቅር በማልሰስትበት አንደበቴ በንፁህ አማራዊ ወንድምነት ምስጋናየ ልባዊ ነው።

ካበረከትኩት በላይ እያመሰግናችው፣ በምሄድበት የስምሪት ቀጠና ሁሉ ለደህንነቴ በቂ ጥበቃና ከለላ እየሰጣችው፣ ለመስጠት ከማይሰስተው እጃችው እና ከማይነጥፈው ኪሳችው ስንቄም ትጥቄም በመሆን ላደረጋችውልኝ መልካም ነገር ሁሉ ከማመስገን ውጭ ሌላ ምንስ ላደርግ እችላለው?

በአንድ አመት ቆይታየ በተለይም በአመራር ስልጠና፣ በማስተማርያና በልዩ ልዩ ዶኮመንት ዝግጅት ብሎም ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ፣ በአደረጃጀት ክለሳወች የበኩሌን አስተዋፅኦ በማበርከት አሁን ላለው ግዙፉ የቴወድሮስ እዝ የበኩሌን አስተዋፅኦ ጠጠር እንደወረወርኩ ይሰማኛል።

አማራ የሚጠነክረውና አሸናፊ ሁኖ የሚወጣው በሚወለደው አማራዊ አንድነት ብቻ መሆኑን ባለኝ ፅኑ እምነት ለአማራ አንድነትም መሪወችን በማናገር፣ ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ አሁን ላለው የአንድነት የተስፋ ብርሃንም የምችለውን ሁሉ እንዳደረኩ ይሰማኛል ለዚህም ሃሳቤን ሳትንቁ ከጎኔ ለነበራችው ለአራቱም ግዛት ከፍተኛ አመራሮች ሁላችውንም ከልብ በመነጨ ትህትና አመሰግናችዋለው።

ሁሉም የቀጠና አደረጃጀቶች ወጥና ተመሳሳይ የአደረጃጀት እና የአመራር አቅም ግንባታ እንዲኖር በማሰብና ያቅሜን አበርክቶ ለማድረግ ወደ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ እዝ በማቅናት በተለይም በአመራር ስልጠና ላይ በማተኮር የበኩሌን አስተዋፅኦ ለማበርከት ድርጅቴን በጠየኩት መሰረት ለተደረገልኝ መልካም ምላሽ ምስጋናየን እያቀረብኩ የቴወድሮስ እዝ ሞያዊይና ወንድማዊ ድጋፌን በጠየቀኝ ወቅት በማንኛውም ሰአትና ቦታ በመገኘት የምችለውን ሁሉ ለማበርከት ዛሬም እንደትናንቱ ዝግጁ መሆኔን ልገልፅ እወዳለው።

ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ እንደመጣው አንተን ማግኘቴ፣ ስንገናኝም ያሳየኸኝ ፍቅርና አክብሮት፣ የጣልክብኝ እምነት በጉዞየ ሁሉ ጉልበቴ ነበርና ሁሌም እንደምለው ፈጣሪ ጥላና ከለላ ሁኖ ለእኛው ለተገፋነው ህዝቦች ሲል የማቱሳላን እድሜ ያድልህ ወንድማለሜ!!!!!

የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ወንድምና እህቶቸ ያደረጋችውልኝ መልካም አበሬታ፣ ድጋፍና ማበረታታት በነበረኝ ቆይታና በቀጣይም ለሚኖረኝ ጉዞ ጉልበቴ ነበርና በያላችውበት ወንድማዊ እና ልባዊ ምስጋናየ ይድረስልኝ።

አርበኛ ዋርካው ምሬ ወዳጆ፣ አርበኛው ወንድሜ ሃብቴ ወልዴ፣ አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ፣ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ አርበኛ መከታው ማሞ፣ ኮል ማነገረው፣ እዮቧ የሸዋው፣ ደርቤ ወሎየው እና ስማችውን ያልጠቀስኳችው ወንድሞቸ ስለሁሉም ወንድማዊ አቀራረባችውና ምክራችው ሁላችውንም ከልብ አመሰግናለው።

በመጨረሻም ለሁሉም የፋኖ አመራሮች የማስተላልፈው ወንድማዊ ምክር

አንድ አለመሆናችን ብዙ የግል ህይወታችን ወደጎን ጥለን በገባን ልክና መጠን የምንታገልለት ህዝባችን እየደረሰበት ያለውን የማያቋርጥ ግፍና መከራ፣ በዱር በገደሉ በየሰአቱ ለሚለዩን እህትና ወንድሞቻችን በአጠቃላይ እንደ ህዝብ አየደረሰ ያለውን ሰቆቃ ለማሳጠርና በአንድ ልብና መንፈስ ተናበንና ተነጋግረን የጋራ በትራችን በጠላት ላይ ለማሳረፍና የሞት አፋፍ ላይ ያለው ጠላታችን በእኛው እንዝላልነት እድል እያገኘ መሆኑን ተገንዝባችውና የሚሄደውን ጠመዝማዛ የአንድነት ጉዞ አሳጥራችው አንድነታችን ባረዘመ ጊዜ እንድታበስሩን ወደማዊ ጥሪየ ነው።

ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!!@


Previous
Previous

ከፋኖ መንደር የተገኙ መረጃዎችና ሌሎችም

Next
Next

አሁን የተሰማው ታሪካዊ ሰበር መረጃ!